የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ተማሪዎች በቤታቸው ሆነው በቴሌቪዥን እንዲማሩ ለማድረግ ዝግጅት ማጠናቀቁን ገለፀ፡፡የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ የቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አዲሱ ሻንቆ ለፋና ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬት እንደተናገሩ የቴሌቪዥን ትምህርት የሙከራ ስርጭት ከሚያዚያ 7 /2012 ዓ/ም ጀምሮ በአፍሪ ሄልዝ የቴሌቪዥን የሚጀምር መሆኑን ገልፀዋል። ለዚህም የመምህራን ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁንም አስታውቀዋል።
የግል ትምህርት ቤቶች ተማሪዎችም በቴሌቪዥን በሚተላለፈው የትምህርት መርሃ ግብር እንደሚካተቱም አቶ አዲሱ ገልፀዋል።በዚህም መሰረት ተማሪዎች በኤፍ ኤም 94 .7 እንዲሁም በአፍሪ ሄልዝ የቴሌቪዥን ጣቢያ የሚሰራጩ የትምህርት ፕሮግራሞች ተማሪዎች አቤት ቁጭ ብለው ሊከታተሉ ይገባል ነው ያሉት።
የ7ኛ እና 8ኛ እንዲሁም 9ኛ እሰከ 12ኛ ክፍል የሒሳብ እና የተ ፈጥሮ ሳይንስ ትምህርት እንዲሁም የ11ኛ እና12ኛ ክፍል የታሪክ “ትምህርት በቤቴ” በሚለው ፕሮግራም በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን እንዲከታተሉም አሳስበዋል።ከ5ኛ እሰከ 8ኛ ክፍል ትምህርት በኤፍ ኤም 94.7 ሬዲዮ ጣቢያ እየተላለፈ መሆኑን ያስታወሱት አቶ አዲሱ ወላጆች በተለይ ተማሪዎች የመማሪያ መጽሀፍት በእጃቸው ላይ ስላለ ትምህርታቸው ላይ ትኩረት በማድረግ እንዲከታተሉ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።
ብሔራዊ ሀገር አቀፈ ፈተናዎችን በተመለከተ ለኮሮና ቨይረሰ የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ የሚፈጸም እንደሆነ አቶ አዲሱ አስታወቀዋል።
Warning: Illegal string offset 'author' in /home/deborahs/public_html/wp-content/themes/education-base/acmethemes/hooks/comment-forms.php on line 17
Warning: Illegal string offset 'email' in /home/deborahs/public_html/wp-content/themes/education-base/acmethemes/hooks/comment-forms.php on line 18
Warning: Illegal string offset 'url' in /home/deborahs/public_html/wp-content/themes/education-base/acmethemes/hooks/comment-forms.php on line 19