ት/ቤታችን የ1ኛ ሩብ ዓመት ትምህርትን ወደ ማጠቃለሉ መድረሱን ስናሳውቃችሁ በታላቅ ደስታ ነው:: በመሆኑም በቀጣይ የሚከናወኑ ኘሮግራሞች እንደሚከተለው መሆኑን እንገልፃለን::

1. ከሰኞ ህዳር 12 – ዕሮብ ህዳር 14፡ 2015 ዓ.ም: የ1ኛ ሩብ ዓመት የማጠቃለያ (ሞዴል ለ6ኛ፡ 8ኛ እና 12ኛ)፡ ፈተና ይሰጣል፡፡ (ት.ቤት ለግማሽ ቀን ብቻ ክፍት ይሆናል)

2. ሐሙስ ህዳር 15 እና አርብ ህዳር 16፤ 2015 ዓ. ም. : መምህራን ሮስተር /የተማሪዎች የፈተና ውጤት / የሚያዘጋጁበት ቀናት ስለሆኑ ት/ቤቱ ለተማሪዎች ዝግ ይሆናል፡፡

3. ሰኞ ህዳር 19 ቀን 2014ዓ.ም የ2ኛው ሩብ አመት ትምህርት ይጀምራል፡፡ ልጅዎ የት/ቤቱን የደንብ ልብስ ለብሶ/ለብሳ አስፈላጊውንም የት/ት ቁሳቁሶችን ይዞ/ዛ እንዲመጣ/ትመጣ ያድርጉ፡፡

4. የመጀመሪያው የወላጅ-የመምህር የምክክር ቀን ቅዳሜ ህዳር 24 ቀን 2015ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰአት እስከ ቀኑ 5፡30 ሰአት ድረስ ይሆናል፡፡ በዚሁ እለት እርሶም ወደ ት/ቤት በመምጣት የልጅዎን ውጤት ገለፃ ያለበት ወረቀትን እንዲወስዱ፣ ስለልጅዎ የትምህርት እንዲሁም የፀባይ ሁኔታ ከክፍል ኃላፊው ጋር እንዲወያዩ፣እንዲሁም በዋነኝነት ስለመማር -ማስተማሩ ያለዎትን አስተያየት እንዲሰጡን ተጋብዘዋል፡፡

ማሳሰቢያ፡ የ2ኛው ሩብ አመት የትምህርት ክፍያ ያልከፈላችሁ ወላጆች የመክፈያ ጊዜ እስከ ህዳር 24፡2015 ዓ.ም መሆኑን እየገለፅን ከህዳር 24፤2015ዓም ጀምሮ ቅጣት የሚጀምር ስለሆነ እባካችሁ በግዜ እንድትከፍሉ እንጠይቃለን፡፡

ት/ቤቱ


Warning: Illegal string offset 'author' in /home/deborahs/public_html/wp-content/themes/education-base/acmethemes/hooks/comment-forms.php on line 17

Warning: Illegal string offset 'email' in /home/deborahs/public_html/wp-content/themes/education-base/acmethemes/hooks/comment-forms.php on line 18

Warning: Illegal string offset 'url' in /home/deborahs/public_html/wp-content/themes/education-base/acmethemes/hooks/comment-forms.php on line 19

Leave a Comment

<